job vacancies in ethiopia

💡 የስራ ማመልከቻ መመሪያዎችን መከተል ለምን አስፈለገ?

እያንዳንዱ ኩባንያ የስራ ማመልከቻዎችን የሚቀበልበት የራሱ የሆነ አሰራር አለው። በማስታወቂያው ላይ የተቀመጡትን ገደቦች ወይም መመሪያዎች አለማክበር፣ ስራ የመቀጠር እድልን ወዲያውኑ ሊያበላሽ ይችላል።

1. የተጠቀሰውን ህግ ማክበር (መመሪያን መከተል)

  • “በስልክ አይጠየቅ” ከተባለ፦ በፍጹም አለመደወል! የሰው ኃይል ክፍል (HR) በስልክ ጥሪዎች እንዳይጨናነቅ ይፈልጋል። ደውለው ከጠየቁ መመሪያ እንደማያከብሩ ነው የሚቆጠረው።

  • “በኦንላይን ፖርታል ብቻ” ከተባለ፦ በድርጅቱ ድረ-ገጽ (Website) ወይም በተጠቀሰው ሊንክ ብቻ ማመልከት። ትተውት በኢሜይል ከላኩ ማመልከቻዎ ውድቅ ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም አውቶማቲክ ሲስተሙ ውስጥ አይገባም።

2. ⚠️ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ “ስልክ ቁጥር” አለመጻፍ!

በፌስቡክ ወይም በቴሌግራም የስራ ማስታወቂያ ሾር “ይሄው ስልኬ፣ ደውሉልኝ” ብሎ ኮሜንት መጻፍ ፍጹም ስህተት ነው፦

  • ቀጣሪዎች በኮሜንት አይደውሉም፦ ድርጅቶች የራሳቸው የቅጥር ስርዓት እንጂ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየፈለጉ የመደወል ልምድ የላቸውም።

  • ለአጭበርባሪዎች መጋለጥ፦ ስልክዎን በይፋዊ ቦታ ላይ መተውዎ ለኢንተርኔት ሌቦች እና ለአጭበርባሪዎች (Scammers) እራስዎን አጋልጠው እንዲሰጡ ያደርጋል።

  • ያልበሰሉ መሆንዎን ያሳያል፦ ይህ ድርጊት ሙያዊ ስነ-ምግባር (Professionalism) እንደጎደለዎትና የስራ ፍለጋ ሂደቱን በቁም ነገር እንዳልወሰዱት ያሳያል።

3. “How to Apply” የሚለውን ክፍል መተግበር

በማንኛውም የስራ ማስታወቂያ መጨረሻ ላይ ማመልከቻው እንዴት፣ የት እና እስከ መቼ መላክ እንዳለበት የሚገልጽ “How to Apply” የሚል ክፍል አለ። እሱን መከተል የሚከተሉትን ጥቅሞች ይሰጣል፦

✔️ ሙያዊ (Professional) መሆንዎን ያሳያል፦ ትናንሽ ዝርዝር ነገሮችን ትኩረት ሰጥተው እንደሚያነቡና መመሪያ መከተል እንደሚችሉ ለቀጣሪው ያረጋግጣል።

✔️ ተፈላጊነትን ይጨምራል፦ በትክክለኛው መንገድ የቀረበ ማመልከቻ በቀላሉ ተለይቶ ስለሚታይ ቀጣሪዎች ቀድመው እንዲመርጡዎት ያደርጋል።

📌 ባጭሩ፦ ስራ ለመቀጠር ብቃት ማሟላት ብቻ በቂ አይደለም፤ ማመልከቻውን ቀጣሪው በፈለገው መንገድ እና ህግ ማቅረብ የመጀመሪያውና ትልቁ ፈተና ነው።

መልካም የስራ ፍለጋ!